እራስን የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲንግ ችሎታን ማስተማሪያ 8 ጠቃሚ ነጥቦች
እራስን የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲንግ ችሎታን ማስተማሪያ 8 ጠቃሚ ነጥቦች
ፕሮግራሚግ በአሁኑ ወቅት በአለማችን ላይ እጅግ በጣም ጠቃሚ እና አዋጪ የሞያ ዘርፍ ነው። እንዲሁም በአለም ላይ
እጅግ በጣም ትልቁን ክፍያ ውይም ደሞዝ ከሚከፈልባቸው ዋና ዋና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የስራ ዘርፎች ግንባር ቀደሙ
ነው። ታዲያ የዚህን ሞያ ችሎታ ለመማር እና ችሎታቹን ለማሳደግ የመጀመርያ ጉዟቹን የጅመራቹ ከሆነ እነኚን እጅግ
በጣም ጠቃሚ እና በትክክለኛው መንገድ ላይ እንድትጓዙ የሚረዳቹ 8 ነጥቦች ይመልከቱ።
እነኚህ ነጥቦች በዚህ
ሞያ ላይ ስኬታማ የሆኑ ግለስቦች ሁሉም በጋራ የሚስማሙበት ነጥቦች ናቸው፤ ታዲያ ይህን ስላቹ ይህ ብቸኛው እካሄድ
ነው ለማለት አይደለም ስኬታማ ፕሮግራመር ለመሆን። ነገር ግን በጉዞዋቹ ላይ ሊያጋጥም ከሚችሉ የግራ መጋባት ሁኔታ
ወይም ሌሎች የሚያጋጥሙ የአካሄድ ችግሮች አንዳይፈጠርባቹህ ይረዳችኋል ማሌቴ ነው።
ነጥብ 1 መጀመሪያ የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ወይም ኮዲግ መማር ለምን እንዳስፈለጋቹ ለይታቹ እወቁት።
ለምሳሌ፦አላማቹ ለገቢ ምንጭ ተሆነ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች የገበያ ሁኔታ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ገበያው
የሚፈልገውን ፕሮግራም ለመለየት እና ትኩረት ሰቶ ለማጥናት። ሌላው ምክንያት ያሚሆነው ደግሞ የእውቀት ደረጃቸውን
ለማስፋት ወይም በትምህርት ውስጥ ሆነው የኮምፒውተር ፕሮግራም እና ተመሳሳይ የትምህርት አይነቶችን በተሳካ ሁኔታ
ፈተናዎችን ለመስራት።
ነገሩ ይህም ሆነ ያ ዋናው እና በጣም ይህን ከማድረጋቹ በፊት ማወቅ የለባቹ ሁለት ነገሮች አሉ።
አንደኛው ነገር የኮምፒውተር ፕሮግራሚግ ለማወቅ ፍላጎት ሊኖራቹሁ አስፈላጊ ነው። ዝም በላቹ በዚህ ሞያ የሚገኘውን
ገቢ ብቻ ለማግኝኘት አስባቹህ ከሆነ ትልቅ ስህተት እየሰራችሁ ነው። ይህ ሞያ የለፍላጎት የሚሰራ ከሆነ ብዙም
መጓዝ የማይቻል ነው ምክንያቱም ብዝዎቹ በዚህ ሞያ የሚሰሩ ስራዎች በራስ ተነሻሽነት የሚሰሩ ናቸው።
ሁለትኛው
ነገር ደግሞ ሰለ ኮምፒውተሮች በቂ ግንዛቤ ሊኖሮት ይገባል። ለምሳሌ፦የኮምፒውተሮች ዋና ዋና ክፍሎችን፤ እያንዳንዱ
ክፍሎች አገልግሎታቸው፤ ክፍሎቹም በምን አይነት መልኩ ስራቸውን እንደሚሰሩ ወይም ምን አይነት ትእዛዞችን በመከተል
የተፈለገውን ስራ እንደሚሰሩ የመሳሰሉትን እና ሌሎችንም ዋና ዋና ስለ ኮምፒውተሮች ማውቅ። ይህ ርእስ በደንብ
የሚያስተምር መጸሀፍ ለማንበብ ከፈለጋቹ introduction to computer science የሚል መጸሀፍ ፈልጋቹ
ማንበብ ትችላላችሁ። በተጨማሪ መሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ማወቅ ያስፈልጋችኋል።
ነጥብ 2 ትክክለኛውን መማር የምትፈልጉትን የፕሮግራሚግ ቋንቋ አይነት ይምረጡ እና ይወስኑ።
ሁለተኛው ደረጃ የሚሆነው የዚህን ችሎታ የፈለጋችሁበት ምክንያት መሰረት በማድረግ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎችን ለይቶ
ማወቅ እና የትኛው የፕሮግራሚግ ቋንቋ ማጥናት እንዳለባቹ ወይም ከየትኛው ቋንቋ ጥናታቹን መጀመር እንዳለባቹ ማወቅ
ያስፈልጋችዋል። ይህን ስላቹ በቴክኖሎጂ አለም ውስጥ ለብዙ አላማ እና ለተለያዩ የኮምፒውተር አይነቶች ወይም
ደረጃዋች የሚጠቅሙ እጅግ በጣም ብዙ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ተፈጥረዋል እንዲሁም ይገኛሉ። ስለዚህ በጣም ጥንቃቄ
በተሞላበት ሁኔታ የትኛው ቋንቋ ለየትኛው አገልግሎት እንደሚውል ለዩ፤ ይህን ግዜ ግራ የሚያጋባ እና እራሳቹ
የመሰላቹን ከማድረግ ይቆጠቡ፤ በIT ወይም በCOMUPTER SCINECE ዘርፍ የተማሩ በቅርብ የሉ ሰዎችን
ይጠይቋቸው፤ ይህን ለማድረግ የማችሉ ከሆነ በኢንተርኔት ይህን ጥያቄ መልስ የሚሰጡ ድረ ገጽ በመመልከት ወይም ስለ
ፕሮግራሚንግ ቋንቋ አይነቶች እና ልይነታቸውን የሚያብራራ መጸሀፎችን እና ድረ ገጾችን መመልከት ትችላላቹሁ በቂ
ግንዛቤ ለማግኘትም ይሞክሩ። ለግንዛቤ ያህል የሚከተለውን ያንብቡት፦
የተለያዩ ቋንቋዎች የተለያየ አገልግሎት አላቸው። ስለዚህ በአይነት ከፋፍለን ማየት እንችላለን ማለት ነው። የተወሰኑት እነዚህ ናቸው፦
Machine languages — interpreted directly in hardware
Assembly languages — thin wrappers over a corresponding machine language
High-level languages — anything machine-independent
System languages — designed for writing low-level tasks, like memory and process management
Scripting languages — generally extremely high-level and powerful
Visual languages — non-text based
ነጥብ 3 ከቲኒሹ ወይም ቀለል ከሚለው የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ይጀምሩ (እና ማጥናት ወይም ማንበብ ከጀመራቹ በኋላ በትእግስት ሳታቋርጡ ለመጨረስ ጥረት አድርጉ )።
እንደ C C++ Python ወይም Ruby ከመሳሰሉት ቀለል ከሚሉት ቋንቋዋች መጀመር የተሻለ ነው።
ነጥብ 4 የመረጣቹሁት የፕሮግራሚግ ቋንቋ መማሪያ መጸሀፍት እና በተግባር የምትለማመዱበት መሳሪያዎችን የዘጋጁ።
ከተለያዩ ድረ ገጾች ላይ የምትፈልጉትን የመማሪያ መሳሪያዎች በነጻ በብዛት ማግኘት ትችላላቹሁ።ከዚህ ድረ ገጽ ብዙ አይነት መጸሀፍትን ያገኛሉ፦
GitHub.com
ነጥብ 5 የጥናት ወቅታቹሁን በሚመች መልኩ በፕሮግራም በስርአቱ የውጡ እና በጽሁፍ የዘጋጁት። የጥናታቹህ ፕሮግራም ቋሚ መሆን አለበት።
ነጥብ 6 በጥናታችሁ ጉዞ ላይ በእያንዳንዱ ከፍሎች ወይም ምእራፎች ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎችን እና ልምምዶችን በተገቢው መልኩ ለመስራት ይሞክሩ።
ለመስራት ያዳገታቹሁን ጥያቄ እንዳታልፉት ተስፋ ሳትቆርጡ ለመስራት ጥረት ያድርጉ የበለጠ እና የተሻለ ግንዛቤ ያገኛሉ።
ነጥብ 7 ሌሎች ይህንን የፕሮግራሚንግ ቋንቋ መማር ፍላጎት ላላችው ግለሰቦች እስከ ተማራቹሁት ድረስ ለማስተማር ይሞክሩ። የተማራቹሁትን ለማስታውስ እና ዘላቂ እውቀት እንድታገኙ የግዛቹሀል።
ነጥብ 8 ሌሎች የሰሩትን ትናኒሽ ፕሮግራም ኮዶችን በመፈለግ የፕሮግራሙን እያንዳንዱን ክፍል በመመራመር እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት ይሞክሩ። ኮዱንም በራሳቹ ለማሻሻል ወይም በመቀያየር ይለማመዱ፡፡
ብዙ #መማር የሚፈልጉ ሰዎች ስላሉ እባክዎ #ሼር ያድርጉት…
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ ያለዎትን እውቀት ያሳድጉ በተጨማሪም በቴሌግራሜ ቻናል ምርጥ ምርጥ ስለኮምፒውተር የምለቃቸውን መረጃዎችን ለመከታተል እንዲያመችዎ ይህንን ይጫኑ https://t.me/MuhammedComputerTechnology በቴሌግራም መከታተል ትችላላችሁ
ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ በፍጥነት መረጃ እንዲደርሳችሁ
Like & share this page
#ሼር_ያድርጉ
#ፔጄን_ላይክ ማድረግዎን አይርሱ