ኦርጂናል(Original) እና ፌክ (ፎርጂድ) ሚሞሪ
(Memory) ካርድ እንዴት መለየት ይቻላል?
ኦርጂናል ሚሞሪ ከፌኩ በምን ይለያል?
1⃣ኛ. ኦርጂናል ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን ውስጥ በማስገባት ፎርማት(Format)
ማድረግ ነው።
✅ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ ምንም ችግር ይጨርሳል።
✅ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኤረር(Error) ቦክስ ያሳያችሁና ይቋረጣል።
2⃣ኛ.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ ወይም በስልኮ ወደ ሚሞሪው ፍይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል።
✅ ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን ፊልም ወይም ሌላ ፍይል ወደ ገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት ማወቅ ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ ይወስዳል
✅ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 – 30 ደቂቃ ሊወስድ ይችላል።
✅ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ ነው ማለት ነው።
3⃣ኛ.ሶስተኛው መንገድ ደሞ ስልካችን ውስጥ በማስገባት ይህን SD insight የተባለ አፕፕ(App) ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን።
✅አፑን ዳውንሎድ ካደረግን በኋላ ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕፕ ስንከፍተው ስለ ሚሞሪው ምርት መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል ነው ማለት ነው።
✅ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የትአይነት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለቴ ነው ።
✅ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም መረጃ አያሳየንም ።
✅ይህ ማለት ሚሞሪው የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው።
✅ስለዚህ የማይታወቅ ሚሞሪ ነው ማለት ነው።