☞ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የማያደርጓቸው #12_ነገሮች:
.
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ሃሳባቸውንና ባህሪያቸውን በመግራት እና ስሜታቸውን በመቆጣጠር ይታወቃሉ፡፡በአዕምሯዊ #ብስለት እና በአስተሳሰብ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች የሚከተሉትን ነገሮች አያደርጉም፡፡
.
➊. ፍርሃት የለባቸውም:
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች #ምክንያታዊ አስተሳሰብን ስለሚያጎለብቱ ሰዎች ብዙ ጊዜ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ህይወታቸው ወደፊት ሊገጥማቸው ስለሚችሉ ችግሮች አስቀድመው ስጋት ውስጥ ለሚጥል ጭንቀት አይዳረጉም፡፡
.
➋. በሌሎች ስዎች ስኬታማነት አይቀኑም:
አዕምሯቸው #ሚዛናዊነትን ያጉለበተ ሰዎች ስኬትን ከተቀዳጁ ሌሎች ሰዎች ትምህርትን ለመውሰድ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንደሆኑ ይነገራል፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች በሌሎች ሰዎች ድክመት እና ስኬትማነት ላይ ማተኮር
የራስን እቅድ ያሳጣል ይላሉ፡፡
.
➌. ባለፈ ነገር አይፀፀቱም:
#ስላለፈው
ጉዳይ መጨነቅ እና በፀፀት ጊዜን ማሳለፍ ለወደፊቱም እቅድን እንዳይነድፉ መሰናክል ይሆናል፤ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች
ካለፈው ችግራቸው ወይም ውድቀታቸው ትምህርት በመውሰድ አሁን ያለውን የተሻለ በማድረግ ለነገ ስኬታማነታቸው በጥረት
ይሰራሉ፡፡
.
➍. ራሳቸውን አሳልፈው አይሰጡም፤ አይሸነፉም:
ብዙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች አካላቸው እንኳ ቢደክም በአስተሳሰብ እና በአመለካከታቸው ብርቱ አቋም ይዘው ለስኬት ይበቃሉ፡፡ ራሳቸውንም ለጠላቶቻቸው አንበርክከው አይሰጡም፡፡
.
➎. ለውጥን አይፈሩም:
እነዚህ ሰዎች ነገሮችን #አመዛዝነው የሚተነብዩ በመሆናቸው በሚያደርጉት ማንኛውም ነገር ለሚመጣው ውጤት ዝግጁ ናቸው፡፡
.
➏. ከአቅማቸው በላይ በሆነ ጉዳይ ጊዜያቸውን አያባክኑም:
በአዕምሯዊ ብስለታቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ሁሉም ነገር እነሱ ባቀዱት ልክ #እንደማይሆን
እና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ስለሚያስቡ አይጨነቁም፡፡ ከአቅማቸው በላይ ሆነው ለጭንቀት የሚዳርጉ
ነገሮችን በአግባቡ በማስተናገድም ካልተገባ ውጥረት ራሳቸውን ያድናሉ፡፡በዚህም ሰኬታማነታቸውን ያጎለብታሉ፡፡
.
➐. ሌሎችን ሰዎች አይለማመጡም:
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች አንድን ነገር ለማድረግ ሌሎችን ሰዎች በመለማማጥ ጊዜያቸውን አያባክኑም፤ አይጨነቁም፡፡ ሰዎችን መለማመጥ፣ ጊዜ እንደሚያባክን፣ ሰዎችን #ጥገኛ
እንደሚያደርግ እና ለግጭት እንደሚዳርግ ስለሚያውቁ ከዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ራሳቸውን ነጻ አድርገው በራስ
መተማመን ይሰራሉ፡፡ በሌሎች ሰዎች ትከሻ ላይ አለመንጠልጠልም በራስ መተማመን እና ጥንካሬን ያዳብራል ብለው
ያስባሉ፡፡
.
➑. ራስን ጥፋተኛ ማድረግ:
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ለራሳቸው የጥፋተኛነት ስሜትን በማስተናገድ አሉታዊ ነገሮች ላይ ረዥም ጊዜ አያባክኑም፡፡ ከዚያ ይልቅ #በአወንታዊ አስተሳብ እና ተግባራት ላይ ያተኩራሉ፡፡ ለመጪው ጊዜ መልካምነትም አበክረው ያቅዳሉ፡፡
.
➒. ተመሳሳይ ስህተት አይሰሩም:
ብዙ ጊዜ ስህተት በድጋሚ ሊከሰት የሚችለው ያለፈውን ካለማገናዘብ እና እንዳይደገም ካለመዘጋጀት እንደሆነ የስነ ልቦና ምሁራን ናገራሉ፡፡ ጥሩ የአዕምሮ ብስለት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ለሚሰሩት ስህተት #ኃላፊነትን በመውሰድ በቀጣይ እንዳይደገም መፍትሔ አስቀምጠው ይሰራሉ፡፡
.
➓. በመጀመሪያው ውድቀታቸው አይሸነፉም:
አዕምሯዊ ጥንካሬ ያላቸው ሰዎች በመጀመሪያው ውድቀታቸው መሸነፍን አያውጁም፤ ከውድቀታቸው ትምህርትን በመውሰድ የተሻለ ውጤትን ለማምጣትም በትጋት ይሰራሉ፡፡
.
➊➊. ቅፅበታዊ ውጤትን አይጠብቁም:
አስተሳሰባቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚሰሩት ስራ #ወዲያውኑ ውጤት እንደሚያስገኝላቸው በማሰብ አይጓጉም፡፡ ከዚህ ይልቅ ሁሉ ስራ የራሱ #ጊዜ
እንዳለው እና የስኬቱም ምንጭ የተቀመጠለት ጊዜ፣ የሚደረግለት ተግባራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን በእቅዳቸው አስቀምጠው
ጉዞ ወደ ፊት ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ምክንያታዊ ወይም እውናዊ የስኬት ምንጭ በአንድ ሌሊት እንደማይመጣ መረዳትን
ያሳያል ነው ያሉት ባለሙያዎቹ፡፡
.
➊➋. ዓለም ሁሉንም ነገር እንድታበረክትላቸው አይፈልጉም:
ዓለማችን ብዙ ተቃርኖዎች ስኬት እና ውድቀት፣ ሀብትና ድህነት፣ ሀዘን እና ደስታ ወዘተ የተጣመሩባት እንደመሆኗ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች #የሚፈልጉትን_ሁሉ ከዓለም እንዲያገኙ አይፈልጉም፡፡ ከዚህ ይልቅ በዓለም ላይ ደስታም ሆነ ሀዘን፣ ስኬትም ሆነ ውድቀት የሚያጋጥመው በራስ ጥረት እና ጥንቃቄ ልክ ነው ብለው ያምናሉ።
………
@ ምንጭ: independent.co (( credit to FBC ))